ስለ ፍርሃት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ፍርሃት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
እኔ ግን ፍርሃት ሲይዘኝ እምነቴን አንተ ላይ አደርጋለሁ
እግዚአብሔር የኃይል እና የፍቅር ራስንም የመግዛት እንጂ፣ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንም፡፡
ያህዌ ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው የሚያስፈራኝ ማን ነው? ያህዌ የሕይወቴ መታመኛዋ ነው የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና፦ "ጽና፥ አይዞህ፥ አትፍራ፥ ተስፋ አትቁረጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"
በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡
ያህዌን ፈለግሁ እርሱም መለሰልኝ ከፍርሃቴም ሁሉ አዳነኝ፡፡
ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።
አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ፣ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።
በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡
ያህዌ ከእኔ ጋር ነው፤ አልፈራም ሰው ምን ሊያደርገኝ ይችላል?
ተመልሳችሁ እንድትፈሩ የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁም። ይልቅ የተቀበላችሁት "አባ፥አባት" ብለን የምንጮህበትን የልጅነትን መንፈስ ነው።
እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡ ስለዚህ ምድር ብትናወጥ ተራሮችም ወደ ባሕር ልብ ቢወሰዱ፣ አንፈራም፡፡
ስለዚህ፣ “ጌታ ረዳቴ ነው፤ አልፈራም። ሰውስ ምን ሊያደርገኝ ይችላል?” ብለን በድፍረት እንናገራለን።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡ ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡