ስለ ሰላም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሰላም የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
በአንተ ታምናለችና በአንተ ለምትጸና አእምሮ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ።
በእምነት ስለ ጸደቅን በጌታችን በኢየሱስ በኩል ከእግዚአብሔር ጋር ሰላም አለን።
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
“ያህዌ ይባርችሁ ይጠብቃችሁ፡፡ ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡ ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’”
ሕፃን ተወልዶልናልና፣ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፣ ኃያል አምላክ፣ የዘላለም አባት፣ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።
በስሜ ሰላም እንዲሆንላችሁ እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ፡፡ በዓለም ውስጥ ስትኖሩ መከራ አለባችሁ ነገር ግን አይዟችሁ፣ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፡፡»
የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
ያህዌ ለሕዝቡ ብርታት ይሰጣል ያህዌ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል፡፡
ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፤ የሰማችሁትንና ያያችሁትን ማናቸውንም ነገር አድርጉ። የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል።
የጽድቅም ሥራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል።
አይሁድንና አሕዛብን ሁለቱን አንድ ሕዝብ ያደረገ እርሱ ሰላማችን ነውና ፤ በሥጋውም እርስ በርስ የለያየንን የጥል ግድግዳ አፈረሰ።
በሰላም የምታኖረኝ አንተ ብቻ ስለሆንህ በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፡፡