ስለ ብቸኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ብቸኝነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኦሪት ዘዳግም 31:6

ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።

02 ዕብራዊያን 13:5

አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።

እግዚአብሔር ብቸኞች በቤተ ሰብ መካከል ያኖራቸዋል፤ እስረኞችን ነጻ አውጥቶ ያስፈነድቃቸዋል፤ ክፉዎች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ፡፡

04 የማቴዎስ 28:20

እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ እንዲያደርጉ እያስተማራችኋቸው፤ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው። እኔም እስከ ዓለም ፍጻሜ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።”

05 ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።

አባትና እናቴ ቢተውኝ እንኳ ያህዌ ይቀበለኛል፡፡

07 ኢሳይያስ 41:13

እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ 'አትፍራ፣ እረዳሃለሁ' ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።

08 ዮሐንስ 14:18

ወላጅ እንደሌላቸው ልጆች አልተዋችሁም፣ ዳግመኛ ወደ እናንተ እመጣለሁ።

ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ፡፡ ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ በዚያ አለህ መኝታዬን በሲኦል ባደርግ በዚያ ትገኛለህ፡፡ በንጋት ክንፍ ተነሥቼ ብበር እስከ ባሕሩ መጨረሻ ብሄድ በዚያም ቢሆን እጅህ ትመራኛለች ቀኝ እጅህም ትይዘኛለች፡፡

አይዞህ! እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድበት ስፍራ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ወደዚያም ምድር በደህና እመልስሃለሁ፤ የገባሁልህን ቃል ኪዳን ሁሉ እፈፅምልሃለሁ፤ ከቶም አልተውህም።"

ተዛማጅ ርዕሶች