ስለ ልብና ስሜቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ቅዱሳት መጻሕፍት ወደ ልብ ስሜቶች ሁሉ በርኅራኄ ይናገራሉ — ፍርሃትና መጽናናት፥ ኀዘንና ደስታ፥ ጭንቀትና ሰላም። የተጨነቃችሁትን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፥ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና። እነዚህ ጥቅሶች የእግዚአብሔርን ቅርበት ወደምትሰማው ስሜት ሁሉ ያመጣሉ።
ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
ብርቱና ደፋር ሁኑ፥ አትፍሯቸው ወይም አትደንግጡል አላቸው። እግዚአብሔር አምላካችሁ ከእናንት ጋር ይሄዳልና አይተዋችሁም አይጥላችሁምም።
ከዚያም ነህምያ እንደዚህ አላቸው፣ “አሁን ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ መልካም ምግብ ተመገቡ ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ መጠጥም ጠጡ፡፡ ከምትበሉትና ከምትጠጡት የሚበሉትና የሚጠጡት ለሌላቸው አካፍሉ፡፡ ይህ ቀን፣ ጌታችንን ለማምለክ የተለየ ቀን ነው፡፡ ሀዘን አይሙላባችሁ! ያህዌ የሚሰጣችሁ ደስታ ብርቱ ያደርጋችኋል፡፡”
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።
ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን! ምክንያቱም የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣም።