ስለ ቁጣ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ቁጣ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 1:19-20

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን! ምክንያቱም የሰው ቊጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያመጣም።

02 ኤፌሶን 4:26-27

«ተቆጡ፤ ነገር ግን ኀጢአት አትሥሩ» በቁጣችሁ ጸሓይ እስከሚገባ ድረስ አትቆዩ፤ ዕድል አትስጡት።

03 ምሳሌ 15:1

የለዘበ መልስ ቁጣን ይመልሳል፣ መጥፎ ቃል ግን ቁጣን ያስነሳል፡፡

04 ምሳሌ 14:29

ትዕግስተኛ ሰው ታላቅ ማስተዋል አለው፣ ለቁጣ የሚቸኩል ሰው ግን ሞኝነትን ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡

05 ቆላስይስ 3:8

አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።

06 ምሳሌ 16:32

ጦረኛ ከመሆን ይልቅ ትዕግስተኛ መሆን ይሻላል፣ መንፈሱን የሚገዛም ከተማን ከሚቆጣጠር ይልቅ ይበረታል፡፡

07 ምሳሌ 29:11

ሞኝ ቁጣውን ሁሉ ይገልጣል፣ ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ይቆጣጠራል፣ ራሱንም ያረጋጋል፡፡

08 መክብብ 7:9

በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና።

አትቆጣ፤ ተስፋም አትቁረጥ መከራን ከማብዛቱ ውጪ ምንም ስለማይጠቅምህ አትከፋ፡፡

10 ምሳሌ 19:11

ጠቢብ አእምሮ ሰውን ታጋሽ ያደርገዋል፣ በደልንም መተው ክብር ይሆንለታል፡፡

11 ያዕቆብ 4:1

በእናንተ መከከል ያለው ፀብና ጭቅጭቅ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ውጊያ ከገጠሙት ክፉ ምኞቶቻችሁ የመጣ አይደለምን?

12 ሮሜ 12:19

የተወደዳችሁ ሆይ ስለራሳችሁ አትበቀሉ ይልቁኑ ለእግዚአብሔር ቁጣ ዕድል ስጡ።ምክንያቱም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፦ «ጌታ 'በቀል የኔ ነው ብድራትን የምከፍለው እኔ ነኝ' ይላል»።

13 ምሳሌ 22:24-25

ግልፍተኛ ሰውን ጓደኛ አታድርግ፣ ቁጣም ካለበት ሰው ጋር አብረህ አትሂድ፣ አለበለዚያ መንገዱን ትማራለህ፣ ራስህንም በወጥመድ ታጠላልፋለህ፡፡

14 የማቴዎስ 5:22

እኔ ግን፣ 'ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ይፈረድበታል፣ ወንድሙን፣ 'አንተ የማትረባ!' የሚለው የሸንጎ ፍርድ፣ 'ቂል' የሚለውም የገሃነመ እሳት ፍርድ ይፈረድበታል።

ተዛማጅ ርዕሶች