ስለ መጽናናት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መጽናናት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2ኛ ቆሮንቶስ 1:3-4

የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።

በጨለማው የሞት ሸለቆ ውስጥ እንኳ ባልፍ አንተ ከእኔ ጋር ስለ ሆንህ ጉዳት ይደርስብኛል ብዬ አልፈራም፡፡

03 የማቴዎስ 5:4

የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና።

የተስፋ ቃልህ ሕያው አድርጐኛልና ይህ በመከራዬ መጽናኛዬ ሆነ፡፡

05 ኢሳይያስ 40:1

"አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ" ይላል አምላካችሁ።

ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡

07 ዮሐንስ 14:16

እኔም ለዘላለም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ እንዲሰጣችሁ አብን እለምናለሁ።

ተዛማጅ ርዕሶች