ስለ ጭንቀት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጭንቀት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን?
የከበድህን ነገር በያህዌ ላይ ጣል እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁን መናወጥ ከቶ አይፈቅድም፡፡
ሰላምን እተውላችኋለሁ፤ ሰላሜንም እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጠው ሰላም ዓለም እንደሚሰጠው ዓይነት አይደለም። ልባችሁ አይጨነቅ፣ አይፍራም።
ሐዘኔ በበዛ ጊዜ፣ ማጽናናትህ ደስ አሰኘኝ፡፡
በሰው ልብ ውስጥ የሚገኝ ጭንቀት ያዋርደዋል፣ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፣ 'አትፍራ፣ እረዳሃለሁ' ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና።
የሰላም ጌታ ራሱ ሁልጊዜ በሁሉ መንገድ ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁም ጋር ይሁን።
እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡
እናንተ ደካሞች፣ ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፣ እኔም ዕረፍት እሰጣችኋላሁ፡፡ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፣ ከእኔም ተማሩ፣ እኔ የዋህና በልቤ ትሁት ነኝ፣ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፡፡ ቀንበሬ ቀላል፣ ሸክሜም የማይከብድ ነው፡፡