ስለ ሥጋት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሥጋት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ስለዚህ ለነገ አትጨነቁ፤ ነገ ለራሱ ይጨነቃልና፡፡ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል፡፡
ስለዚህ ስለ ሕይወታችሁ ምን እንደምትበሉ ወይም ምን እንደምትጠጡ፡- ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ሕይወት ከምግብ፣ ሰውነትስ ከልብስ አይበልጥምን? አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?
ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና። ከማስተዋል በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።
ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ አላቸው፤ "ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ምን እንበላለን ብላችሁ ስለ ሕይወታችሁ ወይም ምን እንለብሳለን ብላችሁ ስለ ሰውነታችሁ አትጨነቁ፡፡ ምክንያቱም ሕይወት ከምግብ ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና፡፡
ነገር ግን በመጀመሪያ መንግሥቱንና ጽድቁን ፈልጉ፤ ከዚያም እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል፡፡
እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።
ከእናንተ መካከል ተጨንቆ በዕድሜው ላይ አንድ ቀን መጨመር የሚችል ይገኛልን?