ስለ ደስታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ደስታ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ከዚያም ነህምያ እንደዚህ አላቸው፣ “አሁን ወደየቤታችሁ ሄዳችሁ መልካም ምግብ ተመገቡ ደስ የሚያሰኝ ጣፋጭ መጠጥም ጠጡ፡፡ ከምትበሉትና ከምትጠጡት የሚበሉትና የሚጠጡት ለሌላቸው አካፍሉ፡፡ ይህ ቀን፣ ጌታችንን ለማምለክ የተለየ ቀን ነው፡፡ ሀዘን አይሙላባችሁ! ያህዌ የሚሰጣችሁ ደስታ ብርቱ ያደርጋችኋል፡፡”
የሕይወትን መንገድ ታሳየኛለህ በአንተ ዘንድ የደስታ ሙላት፣ በቀኝህም የዘላለም ፍስሐ አለ፡፡
ደስታዬ በውስጣችሁ እንዲሆንና ደስታችሁም ፍጹም እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ነግሬአችኋለሁ።
ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ ደግሜም እላለሁ ደስ ይበላችሁ።
የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፣ ሠላም፣ ትዕግሥ፣ ቸርነት፥ መልካምነት፥ እምነት፥
ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡
በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በተስፋ ትሞሉ ዘንድ የተስፋ አምላክ በማመናችሁ ምክንያት በደስታና በሰላም ሁሉ ይሙላችሁ።
ወንድሞቼ ሆይ፣ በልዩ ልዩ ፈተናዎች ውስጥ ማለፋችሁን እጅግ ደስ እንደሚያሰኝ ነገር ቊጠሩት፡፡ በፈተና ውስጥ ሳላችሁ በእግዚአብሔር ስታምኑ ይበልጥ ሌሎች ፈተናዎችን በትዕግሥት ለማሳለፍ የሚረዱዋችሁ መሆኑን ትረዳላችሁ፡፡
በእንባ የሚዘሩ በእልልታ ይዘራሉ
ኢየሱስ ክርስቶስን ባታዩትም እንኳ ትወዱታላችሁ፤ አሁን ባታዩትም በእርሱ ታምናላችሁ፤ ሊነገር በማይቻልና ክብር በሞላበት ሐሤት በጣም ደስ ይላችኋል፤
ውኃውንም ከመድኃኒት ምንጮች በደስታ ትቀዳላችሁ።
ጻድቃን ሆይ፣ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ ልበ ቅኖች ሆይ፣ እልል በሉ፡፡
ይህም ሁሉ ቢሆን፣ እኔ በያህዌ ደስ ይለኛል በመድኃኒቴም አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመንፈስ ቅዱስ የሚሆን ጽድቅ፥ ሠላምና ደስታ እንጂ የመብልና የመጠጥ ጉዳይ አይደለም።
ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፣