ስለ ሐዘን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሐዘን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡
የሚያዝኑ የተባረኩ ናቸው፤ ይጽናናሉና።
ኢየሱስ አለቀሰ፡፡
እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ሞት፣ ወይም ሐዘን፣ ወይም ለቅሶ ወይም ሕመም አይኖርም። ምክንያቱም የቀድሞ ነገሮች አልፈዋል።
ወንድሞች ሆይ፣አንቀላፍተው ስላሉት ባለማወቃችሁ ስለወደፊቱ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ሀዘናችሁ መሪር እንዲሆን አንፈልግም።
ቁጣው ለአጭር ጊዜ ነው ሞገሱ ግን ለዕድሜ ልክ ነው፡፡ ሌሊት ሲለቀስ አድሮ ማለዳ ደስታ ይሆናል፡፡
የተናቀ ከሰውም የተጠላ፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው። ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፣ እኛም አላከበርነውም።
ያህዌ ሆይ፣ ጭንቀት ውስጥ ነኝና ማረኝ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል፡፡
የምህረት አባት፥ የመፅናናት አምላክ እና በመከራችን ሁሉ የሚያፅናናን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እግዚአብሔር በመከራችን ሁሉ ያፅናናል፥እኛም ራሳችን በእርሱ በእግዚአብሔር በተፅናናንበት መፅናናት ልክ ሌሎችን ማፅናናት እንችላለን።
የመንከራተት ቀኖቼን ቆጥረሃል እንባዎቼን በመያዣህ አኑረሃል፡፡ ሁሉስ በመጽሐፍህ ያለ አይደለምን?
«ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔ ደግሞ እመኑ።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፣ በአመድ ፋንታ አክሊልን፣ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፣ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
ልባቸው የተሰበረውን ይፈውሳል ቁስላቸውንም ይጠግናል፡፡