ስለ ምስጋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ምስጋና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 1 ተሰሎንቄ 5:18
ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና።
በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፡፡ አመስግኑት ስሙንም ባርኩ፤
03 ቆላስይስ 3:17
በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
04 ኤፌሶን 5:20
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ
ቸር ነውና ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ያህዌን አመስግኑ፡፡
ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
07 ያዕቆብ 1:17
ማንኛውም መልካምና ፍጹም ስጦታ እንደሚዘዋወር ጥላ ከማይለዋወጠው ከላይ ከሰማይ ከብርሃናት አባት ይወርዳል።