ስለ ተስፋ ማጣት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ተስፋ ማጣት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ነፍሴ ሆይ፣ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ በውስጤ ትታወኪያለሽ? የመድኃኒቴን አምላክ ዳግመኛ እንዳመሰግነው እግዚአብሔርን ተስፋሽ አድርጊ፡፡

02 2ኛ ቆሮንቶስ 4:8-9

በሁሉ መንገድ መከራን እንቀበላለን፥ሆኖም በዚያ አንዋጥም። እናመነታለን ነገር ግን ተስፋ በማጣት አንረበሽም። ቢሆንም ግን ተረስተን አንቀርም።

ያህዌ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው መንፈሳቸው የደቀቀውንም ያድናቸዋል፡፡

ነገር ግን ይህን አስባልሁ፥ ተስፋ ሊኖረኝ የቻለውም ከዚህ የተነሳ ነው። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!

በትዕግሥት ያህዌን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማኝ፡፡ ከአደገኛ ጉድጓድ፣ ከሚያዘቅጥም ጭቃ አወጣኝ፤ እግሮቼን፣ በዐለት ላይ አቆመ አካሄዴንም አጸና፡፡

በሕያዋን ምድር የያህዌን መልካምነት እንደማይ ባላምን ኖሮ ምን እሆን ነበር? እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ አይዞህ በርታ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ

07 ሮሜ 8:38-39

ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።

ሥጋዬና ልቤ ደከሙ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም የልቤ ብርታትና አለኝታ ነው፡፡

ጠላቴ፣ ሆይ ብወድቅ እንኳ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ከወደቅሁበት እነሣለሁ በጨለማ ብቀመጥ እንኳ ያህዌ ብርሃን ይሆንልኛል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች