ስለ አለመተማመን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አለመተማመን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤርሚያስ 1:5

"በማኅፀን ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብ ነቢይ አድርጌሃለሁ።"

ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ ሥራህ እጅግ ድንቅ ነው ነፍሴም ይህን በሚገባ ታውቃለች፡፡

03 ኤፌሶን 2:10

ምክንያቱም እግዚአብሔር ከዘመናት በፊት እንድንፈጽመው ያዘጋጀውን መልካም ሥራ ለመሥራት በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጠርን የእግዚአብሔር እጅ ሥራዎች ነን።

04 ፊልጵስዩስ 1:6

ይህን መልካም ሥራ በእናንተ ውስጥ የጀመረው ኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚመለስ ቀን ድረስ እንደሚፈጽም እርግጠኛ ነኝ።

05 2ኛ ቆሮንቶስ 12:9

እርሱም፣ «ጸጋዬ ይበቃሃል ኃይል በድካም ይፈጸማልና» አለኝ። ስለሆነም የክርስቶስ ኃይል ያርፍብኝ ዘንድ አብዝቼ ስለ ድካሜ እመካለው።

06 ኤርሚያስ 17:7-8

ነገር ግን በእግዚአብሔር የታመነ፣ የልበ-ሙሉነቱ ምክንያት እግዚአብሔር ነውና ቡሩክ ነው። በውኃ አጠገብ እንደ ተተከለ፣ በወንዝም ዳር ሥሩን እንደሚዘረጋ ተክል ይሆናልና። ሙቀት ሲመጣ አያይም፣ ቅጠሉ ይለመልማልና። ከዚያም፣ በድርቅ ዓመት ላይ አይሠጋም፣ ማፍራቱንም አያቋርጥም።

07 ገላቲያ 2:20

ከክርስቶስ ጋር ተሰቅያለሁ። ከእንግዲህ የምኖረው እኔ አይደለሁም፥ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል። አሁን በሥጋ የምኖረው ኑሮ በወደደኝና እራሱን ስለ እኔ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው።

08 1ኛ ዬሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።

09 ኢሳይያስ 43:1

አሁንም ያዕቆብ ሆይ፣ የፈጠረህ፣ እስራኤልም ሆይ፣ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፣ አንተ የእኔ ነህ።

10 ሮሜ 8:38-39

ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።

11 ሶፎንያስ 3:17

አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡

12 ቆላስይስ 2:10

በእርሱም ተሞልታችኋል። እርሱ የአለቅነትና የሥልጣን ሁሉ ራስ ነው።

13 1ኛ ቆሮንቶስ 1:27

ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ።

ኅይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቃና እግዚአብሔር ነው።

15 ኤፌሶን 1:4

እግዚአብሔር በክርስቶስ የምናምነውን እኛን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት መርጦናል። ይህም በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን እንሆን ዘንድ ነው

ተዛማጅ ርዕሶች