ስለ የእግዚአብሔር እንክብካቤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር እንክብካቤ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 የማቴዎስ 6:26

አየር ላይ የሚበርሩ ወፎችን ተመልከቱ! እነርሱ እህል አይዘሩም ወይም አያጭዱም፣ በጐተራም አያከማቹም፤ ይሁን እንጂ፣ የሰማይ አባታችሁ ይመግባቸዋል፡፡ ከወፎች ይልቅ እናንተ እጅግ የሚበልጥ ዋጋ ያላችሁ አይደላችሁምን?

02 1ኛ ጴጥሮስ 5:7

እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

03 የማቴዎስ 6:31-32

እንግዲህ ‹ምን እንበላለን?› ወይም ‹ምን እንጠጣለን?› ወይም ‹ምን እንለብሳለን?› ብላችሁ አትጨነቁ፡፡ አሕዛብ እነዚህን ሁሉ ይፈልጋሉና፤ የሰማይ አባታችሁ እነዚህ ሁሉ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል፡፡

የከበድህን ነገር በያህዌ ላይ ጣል እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁን መናወጥ ከቶ አይፈቅድም፡፡

05 ሉቃስ 12:7

ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ፀጉሮች እንኳ የተቈጠሩ ናቸው። አትፍሩ፣ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች የላቀ ዋጋ አላችሁ።

06 የማቴዎስ 10:29-31

ሁለት ድንቢጦች በትንሽ ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ሆኖም አንዷም ብትሆን አባታችሁ ሳያውቅ በመሬት ላይ አትወድቅም፡፡ የእናንተ ግን የራሳችሁ ጠጉር እንኳን ሳይቀር የተቈጠረ ነው፡፡ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች የበለጠ ዋጋ አላችሁ፡፡

07 ኢሳይያስ 41:10

እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።

ያህዌ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል እርሱ ሕይወትህንም ይጠብቃል፡፡ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌ በምታደርገው ሁሉ ይጠብቅሃል፡፡

09 ትንቢተ ናሆም 1:7

ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡

እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ ጌታ ግን ያስብልኛል፡፡ አንተ ረዳቴ ነህ እኔን ለማዳን ፍጠን አምላኬ ሆይ አትዘግይ፡፡

11 ኢሳይያስ 46:4

እስከ ሽምግልና ድረስ እኔ ነኝ፣ እስከ ሽበትም ድረስ እሸከማችኋለሁ፤ እኔ ሠርቻለሁ እኔም አነሣለሁ፤ እኔ እሸከማለሁ እኔም አድናለሁ።

12 1ኛ ጴጥሮስ 5:6-7

እርሱ በወሰነው ጊዜ ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከእግዚአብሔር ብርቱ እጅ በታች ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱ ስለ እናንተ ስለሚያስብ የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።

አምላኬ ሆይ፣ ለእኔ ያለህ ሐሳብ እንዴት ግሩም ነው! ቁጥሩስ ምንኛ የበዛ ነው! ልቁጠራቸው ብል ከአሸዋ ቁጥር ይበልጣሉ ተኛሁ ነቃሁም፤ ያም ሆኖ ግን አሁንም ከአንተው ጋር ነኝ፡፡

ሙሴ ስለ ብንያም እንዲህ አለ፦ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ በእርሱ ተጠብቆ በሰላም ይረፍ፤ ቀኑን ሙሉ ይጋርደዋልና፤ እግዚአብሔር የሚወደውን ሰው በትክሻዎቹ መካከል ያርፋል።

ተዛማጅ ርዕሶች