ስለ የአባት ልብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የአባት ልብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ሉቃስ 15:20

ስለዚህ ታናሹ ልጅ ተነሥቶ ወደ አባቱ መጣ። ልጁ ገና ከሩቅ እየመጣ ሳለ፤ አባቱ አይቶ በርኅራኄ ሮጦ ተቀበለውና ዐቅፎ ሳመው።

02 ሉቃስ 15:7

እንዲሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኅጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ እንደሚሆን እነግራችኋለሁ።

03 ሶፎንያስ 3:17

አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡

04 1ኛ ዬሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።

አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ያህዌም ለሚፈሩት ይራራል፡፡

06 የማቴዎስ 7:11

እንግዲህ፥ እናንተ ክፉዎች የሆናችሁ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ፥ በሰማይ የሚኖር አባታችሁ ለሚለምኑት አብዝቶ መልካም ስጦታን እንዴት አይስጣቸውም?

በተቀደሰ ማደሪያው ያለው አምላክ አባት ለሌላቸው አባት ነው፡፡ ለመበለቶችም ዳኛ ነው፡፡

08 ሆሴዕ 11:1

እስራኤል ወጣት በነበረበት ጊዜ ወደድኩት፥ ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት።

ተዛማጅ ርዕሶች