ስለ የእግዚአብሔር ታማኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር ታማኝነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!

02 ኦሪት ዘዳግም 7:9

ስለዚህ እግዚአብሔር አምላካችሁ እርሱ አምላክ እንደ ሆነ ለሚወድዱትና ትእዛዘትንም ለሚጠብቁት፥ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆን እወቁ፥

03 1ኛ ቆሮንቶስ 1:9

ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

04 2 ጢሞቴዎስ 2:13

ባናምነው እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፣ ራሱን ሊክድ አይችልምና፡፡

ያህዌ ሆይ፣ ታማኝነትህ እስከ ሰማይ እውነተኛነትህም እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡

የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ እንደ አንተ ያለ ኃያል ማነው? ታማኝነትህም ከቦሃል፡፡

07 ዕብራዊያን 10:23

ተስፋን የሰጠ እግዚአብሔር ታማኝ ስለሆነ፣ አምነን የምንመሰክረውን ተስፋ ያለ ማወላወል አጥብቀን እንያዝ።

ተዛማጅ ርዕሶች