ስለ ምሕረት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ምሕረት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 2:4-5

ነገር ግን እግዚአብሔር ምሕረት በማድረግ ባለጠጋ ስለሆነ፥ ከወደደን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ በበደላችን ሙታን በነበርንበት ጊዜ እንኳ ከክርስቶስ ጋር አዲስ ሕይወት ሰጠን፤የዳናችሁትም በጸጋ ነው፤

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!

03 ቲቶ 3:5

ከምህረቱ የተነሳ፣ በአዲስ ልደት መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ መታድስ አዳነን እንጂ፣ በሠራነው የጽድቅ ሥራ ምክንያት አይደለም።

04 ዕብራዊያን 4:16

ስለዚህ በሚያስፈልገን ጊዜ ምሕረትንና የሚረዳንን ጸጋ እንድንቀበል ወደ ጸጋው ዙፋን በድፍረት እንቅረብ።

ኃጢአትን ይቅር የሚል የርስቱንም ትሩፍ መተላለፍ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? የኪዳን ታማኝነትህን ለእኛ ማሳየት ደስ ስለሚልህ አንተ ለዘላለም አትቆጣም፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች