ስለ የእግዚአብሔር ፍቅር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ የእግዚአብሔር ፍቅር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 1ኛ ዬሐንስ 4:10

ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡

02 ዮሐንስ 3:16

በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፤

03 ሮሜ 5:8

ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች እያለን ክርስቶስ ስለ እኛ መሞቱ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያረጋግጣል።

04 1ኛ ዬሐንስ 3:1

የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን እንድንጠራ፣አብ የሰጠን ፍቅር ፣ምን ዓይነት እንደሆነ አስተውሉ ፤ እኛም ልክ እንደዛው ነን! በዚህ ምክንያት ዓለም እርሱን እንደማያውቀው እኛንም አያውቀንም።

05 ሮሜ 8:38-39

ሞት ቢሆን ሕይወት፥ መላእክት ቢሆኑ መንግሥታት፥አሁን ያሉት ነገሮች ወይም ሊመጡ ያሉት ቢሆኑ፥ ኃይላት ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን ዝቅታ፥ የትኛውም ሌላ ፍጥረት ቢሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየኝ እንደማይችል ተረድቻለሁ።

06 ኤፌሶን 3:18-19

ደግሞም የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፥ርዝመቱ፥ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር መረዳት ትችሉ ዘንድ ነው። እንዲሁም በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ፥ ከሰው ዕውቀት ሁሉ በላይ የሆነውን የክርስቶስን ታላቅ ፍቅር እንድታውቁ ነው።

07 1ኛ ዬሐንስ 4:16

እኛም እግዚአብሔር ለኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል ደግሞም አምነናል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፣እግዚአብሔርም በርሱ ይኖራል፡፡

08 ሶፎንያስ 3:17

አንቺን ለማዳን ብርቱ የሆነው አምላክሽ ያህዌ በመካከልሽ ነው፡፡ በአንቺ እጅግ ደስ ይለዋል፤ በፍቅሩም ያሳርፍሻል፡፡ በዝማሬ በአንቺ ደስ ይለዋል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች