ስለ ርኅራኄ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ርኅራኄ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 6 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ ያህዌም ለሚፈሩት ይራራል፡፡

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር የኪዳኑ ታማኝነት የተነሳ ነው፥ የምሕረቱ ሥራዎች አያልቁምና። የምሕረቱ ሥራዎች ማለዳ ማለዳ አዲስ ናችው፤ ታማኝነትህ ምንኛ ታላቅ ነው!

ያህዌ ቸር ነው፤ ርኅሩኅም ነው ለቁጣ የዘገየ ምሕረቱም የበዛ ነው፡፡

04 የማቴዎስ 9:36

ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው።

05 ኢሳይያስ 49:15

"በውኑ ሴት ከማኅፀንዋ ለተወለደው ልጅ እስከማትራራ ድረስ ሕፃንዋን ትረሳ ዘንድ ትችላለችን? አዎን፣ እርስዋ ትረሳ ይሆናል፣ እኔ ግን አልረሳሽም።

ያህዌ ቸርና መሐሪ ነው፡፡ አምላካችን ርኅሩኅ ነው፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች