ስለ መጠጊያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መጠጊያ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኃይላችን፣ በመከራም ቀን ረዳታችን ነው፡፡
ሰዎች ሆይ፣ ሁልጊዜ በእርሱ ታመኑ በፊቱም ልባችሁን አፍስሱ እግዚአብሔር ለእኛ መጠጊያችን ነውና፡፡ ሴላ
የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡
ያህዌ ለተጨቆኑት ዐምባ ነው፡፡ በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል፡፡
ያህዌ መልካም ነው፤ በመከራ ጊዜም መሸሸጊያ ነው፤ በእርሱ ለሚታመኑበት ታማኝ ነው፡፡
ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡
ያህዌ ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እርሱ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው፡፡
አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራም ታወጣኛለህ፡፡ በድል ዝማሬ ትከበኛለህ፡፡ ሴላ
አንተ መጠጊያዬ ከጠላትም የምከለልብህ ፅኑ ግንብ ሆነኸኛልና፡፡ በማደሪያህ ለዘላለም ልኑር በክንፎችህም ጥላ ልከለል፡፡ ሴላ
ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ እጮኻለሁ «አንተ መጠጊያዬ ነህ በሕያዋን ምድር ዕድል ፈንታዬ ነህ» እላለሁ፡፡
ዘላለማዊ አምላክ መኖርያህ ነው፤ የዘላለም ክንዶቹም ከበታችህ ናቸው፤ እርሱን አጥፋው! በማለት፤ ጠላትህን ከፊትህ ያስወግደዋል።
ያህዌ ሆይ፣ አንተን ተማጽኛለሁና እፍረት ከቶ አይድረስብኝ፤ በጽድቅህም ታደገኝ፡፡ ጌታ ሆይ፣ አድምጠኝ ፈጥነህም ታደገኝ የመማጸኛ ዐለት፣ የመዳኛም ምሽግ ሁነኝ፡፡
እግዚአብሔር የምጠጋበት ዐለቴ፣ ጋሻዬና የድነቴ ቀንድ ነው፡፡ እርሱም ጠንካራ ምሽጌ፣ መጠጊዬና ከግፍ የሚያድነኝ ነው፡፡