ስለ መገላገል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መገላገል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ጻድቃን ወደ ያህዌ ይጮኻሉ እርሱም ይሰማቸዋል፤ ከመከራቸውም ሁሉ ያድናቸዋል፡፡
ያህዌ ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፡፡ እርሱ አምላኬ የምሸሸግበት ዐለቴ፣ ጋሻዬ፣ የድነቴ ቀንድና ዐምባዬ ነው፡፡
ከብርቱ ጥፋት አዳነን እንዲሁም ያድነናል። መታመናችንን በእርሱ ላይ አድርገናል፤እርሱም ይታደገናል።
በትዕግሥት ያህዌን ደጅ ጠናሁት እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማኝ፡፡ ከአደገኛ ጉድጓድ፣ ከሚያዘቅጥም ጭቃ አወጣኝ፤ እግሮቼን፣ በዐለት ላይ አቆመ አካሄዴንም አጸና፡፡
05 ዳንኤል 6:27
እርሱ ይታደጋል፣ ያድናልም በሰማይና በምድር ምልክቶችንና ድንቆችን ያደርጋል ዳንኤልን ከአንበሶች አፍ አድኖታል።
ያህዌን ፈለግሁ እርሱም መለሰልኝ ከፍርሃቴም ሁሉ አዳነኝ፡፡
በተጨነቁ ጊዜ ወደ ያህዌ ጮኹ እርሱም ከመከራቸው አዳናቸው፡፡
08 2 ጢሞቴዎስ 4:18
ጌታ ከክፉ ሥራዎች ሁሉ አውጥቶኛል፣ ለሰማያዊውም መንግሥቱ ይጠብቀኛል፡፡ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፡፡ አሜን፡፡
በመከራ ቀን ጥራኝ እኔ እታደግሃለሁ፤ አንተም ታከብረኛለህ፡፡
10 ቆላስይስ 1:13
ከጨለማ ኅይል አዳነን፤ ወደ ተወደደውም ወደ ልጁ መንግሥት አሸጋገረን።