ስለ መንፈሳዊ ውጊያ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መንፈሳዊ ውጊያ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ውጊያችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከአለቆች፥ ከሥልጣናት፥ ከዚህ ከጨለማ ዓለም ገዦችና በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ርኩሳን መናፍስት ጋር ነው።
በክፉ ቀን ክፉውን በመቃወም ጸንታችሁ ትቆሙ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ፤ ጸንታችሁ ለመቆምም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ አድርጉ። ወገባችሁን በእውነት ቀበቶ ታጥቃችሁ፥የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ ጸንታችሁ ቁሙ፤
የምንዋጋባቸው የጦር መሳሪያዎች ሥጋዊ አይደሉምና ይልቁንም ምሽጎችን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለቸው ፥ አሳሳች የሆኑ ክርክሮችንም ያፈርሳሉ። ደግሞም በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ የሚነሳውን ከፍ ያለውን ነገር ሁሉ እናፈርሳለን ፥ እንዲሁም ለክርስቶስ ለመታዘዝ ሀሳብን ሁሉ እንማርካለን።
ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል።
ጠንቃቆች ሁኑ፤ ንቁም፤ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሳ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራል። በዓለም ዙሪያ ያሉ ወንድሞቻችሁ ተመሳሳይ መከራ እንደሚቀበሉ ዐውቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት።
የዲያብሎስን ተንኮል አዘል ዕቅድ መቋቋም ትችሉ ዘንድ የእግዚአብሔርን የጦር ዕቃ ሁሉ ልበሱ።
የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ውስጥ በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።