ስለ ጥበቃ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ጥበቃ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡ ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡
ያህዌ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል እርሱ ሕይወትህንም ይጠብቃል፡፡ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም ያህዌ በምታደርገው ሁሉ ይጠብቅሃል፡፡
03 ኢሳይያስ 41:10
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና፣ አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፣ እረዳህማለሁ፣ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።
04 2ኛ ተሰሎንቄ 3:3
ነገር ግን የሚያጸናችሁና ከክፉው የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።
አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራም ታወጣኛለህ፡፡ በድል ዝማሬ ትከበኛለህ፡፡ ሴላ
ዐይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ ረዳቴ ከወዴት ይመጣል? ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከያህዌ ዘንድ ይመጣል፡፡ እግርህ እንዲንሸራተት አይፈቅድም አንተን የሚጠብቅህም አይተኛም፡፡
07 ምሳሌ 18:10
የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ወደ እርሱ ሮጦ ይድናል፡፡