ስለ እግዚአብሔር ጋሻችን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እግዚአብሔር ጋሻችን የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ያህዌ ብርታቴና ጋሻዬ ነው ልቤ በእርሱ ይተማመናል፤ እርሱም ረዳኝ፡፡ ስለዚህ ልቤ ሐሤት አደረገ፤ በዝማሬም አመሰግነዋለሁ፡፡
ከዚህ በኋላ የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ አብራም መጣ፤ “አብራም ሆይ፣ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ታላቅ ሽልማትህም እኔው ነን።”
አንተ ግን ያህዌ ሆይ፣ ዙሪያዬን እንደ ጋሻ ትከልለኛለህ፣ ክብሬንና ራሴንም ከፍ የምታደርግ አንተ ነህ፡፡
የእግዚአብሔር መንገድ ፍጹም ነው፤ የያህዌ ቃል የነጠረ ነው። መጠጊያ ለሚያደርጉት ሁሉ እርሱ ጋሻ ነው።
05 ምሳሌ 30:5
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ ተፈትኗል፣ በእርሱ ለሚታመኑ ጋሻ ነው፡፡
አምላካችን ያህዌ ፀሐይና ጋሻችን ነውና፤ ያህዌ ጸጋንና ክብርን ይሰጣል፤ በቅንነት የሚሄዱትን መልካም ነገር አይነፍጋቸውም፡፡
ያህዌን በተስፋ እንጠብቃለን እርሱ ረድኤታችንና ጋሻችን ነው፡፡
አንተ ጋሻዬና መሸሸጊያ ነህ ቃልህን በተስፋ እጠብቃለሁ፡፡