ስለ መልካም ንግግር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መልካም ንግግር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ቆላስይስ 4:6

ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።

02 ኤፌሶን 4:29

ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።

03 ምሳሌ 15:4

ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡

ዐለቴና አዳኜ ያህዌ ሆይ፣ የአፌ ቃልና የልቤም ሐሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን፡፡

05 ምሳሌ 16:24

ደስ የሚያሰኙ ቃላት የማር ወለላ ናቸው፣ ለነፍስ የሚጣፍጡ አጥንትንም የሚፈውሱ ናቸው፡፡

06 ምሳሌ 10:11

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው አፍ የሕይወት ምንጭ ነው፣ የክፉ ሰው አፍ ግን ጥፋትን ይደብቃል፡፡

07 ምሳሌ 10:20-21

የጻድቅ ሰው ምላስ የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ዋጋ የለውም፡፡ የጻድቅ ሰው ከንፈሮች ብዙ ሰዎችን ያንጻሉ፣ ሞኞች ግን ባለማማዛዘናቸው ምክንያት ይሞታሉ፡፡

08 ምሳሌ 25:11

በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡

09 የማቴዎስ 12:34-35

እናንተ የእባብ ልጆች ክፉዎች ስለ ሆናችሁ፣ እንዴት መልካም ልትናገሩ ትችላላችሁ? ምክንያቱም በልብ ውስጥ የሞላውን አፍ ይናገረዋል፡፡ . መልካም ሰው በልቡ ውስጥ ካለው መልካም መዝገብ፣ መልካሙን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ልቡ ውስጥ ካለው ክፉ መዝገብ ክፉውን ይወጣል።

10 ምሳሌ 16:23

የጥበበኛ ሰው ልብ ለአፉ ትምህርትን ይሰጠዋል፣ ለከንፈሮቹም ትምህርትን ይጨምራል፡፡

11 ኤፌሶን 5:4

ጸያፍ ንግግር፥ዋዛ ወይም ውርደትን የሚያስከትል ቀልድ ለእናንተ ስለማይገባ ከመካከላችሁ አስወግዱ፤ከዚህ ይልቅ የምታመሰግኑ ሁኑ።

12 ምሳሌ 15:23

ሰው ተገቢ የሆነ መልስ ሲሰጥ ደስታን ያገኛል፤ የጊዜው ቃል ምንኛ መልካም ነው!

13 ያዕቆብ 3:10

ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣል። ወንድሞቼ፣ እንዲህ መሆን የለበትም።

14 ምሳሌ 12:14

ሰው ከቃሎቹ ፍሬ የተነሳ መልካም ነገርን ይጠግባል፣ እንደ እጁ ስራም ዋጋውን ይቀበላል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች