ስለ ስም ማጥፋት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ስም ማጥፋት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ኤፌሶን 4:31

ሁሉ፥ቁጣንና ንዴትን፥ጭቅጭቅንና ስድብን ከማንኛውም ዓይነት ክፋት ጋር ከእናንተ ዘንድ አስወግዱ።

ባልንጀራውን በስውር የሚያማውን አጠፋለሁ፡፡ ትዕቢተኛ ዐይንና እብሪተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም፡፡

03 ቲቶ 3:2

ማንንም እንዳይሳደቡ፣ የሌሎችንም ፈቃድ እንዲያከብሩ እንጂ እንዳይከራከሩ፣ ለሁሉም ሰው ትህትን እንዲያሳዩ አሳስባቸው።

04 ያዕቆብ 4:11

ወንድሞች ሆይ፣ እርስ በርስ አትወነጃጀሉ። ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሕጉ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በእግዚአብሔርም ሕግ ላይ ይፈርዳል። ሕጉ ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ ፈራጆች እንጂ፣ ሕጉን አድራጊዎች አይደላችሁም።

05 ምሳሌ 10:18

ጥላቻን የሚደብቅ ሰው ሐሰተኛ ከንፈሮች አሉት፣ ሐሜትን የሚያስፋፋ ሞኝ ነው፡፡

ያህዌ ሆይ፣ በድንኳንህ ውስጥ የሚያድር ማን ነው? በተቀደሰው ኮረብታህስ የሚኖር ማን ነው? አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤ በአንደበቱ የማይሸነግል ሌሎች ሰዎችን የማይጐዳ፤ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታ የማያሰራጭ

07 1ኛ ጴጥሮስ 2:1

እንግዲህ ክፋትን ፣ ማታለልን ፣ ግብዝነትን፣ ቅናትንና ሐሜትን ሁሉ አስወግዱ።

08 ቆላስይስ 3:8

አሁን ግን ቁጣን፤ ንዴትን፤ ተንኮልን፤ ስም ማጥፋትን ከእናንተ አስወግዱ፤ የሚያሳፍር ንግግርም ከአፋችሁ አይውጣ።

09 ምሳሌ 16:28

ጠማማ ሰው ጥልን ያነሳሳል፣ ሐሜትም የቅርብ ወዳጆችን ያለያያል፡፡

10 ዘጸአት 23:1

ማንም ሰው የሐሰት ወሬ እትናገር። ሐሰተኛ ምስክር ለመሆን ከክፉ ሰው ጋር አትተባበር።

11 የማቴዎስ 15:19

ከልብ ክፉ ዐሳብ፣ ነፍስ መግደል፣ ምንዝርና፣ ዝሙት፣ ስርቆት፣ የሐሰት ምስክርነትና ስድብ ይወጣሉ፤

ተዛማጅ ርዕሶች