ስለ እውነትን መናገር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ እውነትን መናገር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ኤፌሶን 4:15
ይልቁንም እውነትን በፍቅር የምንናገር እና ራስ ወደ ሆነው ወደ ክርስቶስ በሁሉም መንገድ የምናድግ ሰዎች መሆን ይጠበቅብናል።
02 ዘካርያስ 8:16
እናንተ ማድረግ ያለባችሁ እነዚህን ነው፤ እርስ በርሳችሁ እውነትን ተነጋገሩ፤ በአደባባዮቻችሁም እውነትን፣ ፍትሕንና ሰላምን አስፍኑ።
03 ኤፌሶን 4:25
ውሸትን አስወግዱ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ስለሆንን «እያንዳንዱ ከባልንጀራው ጋር እውነትን ይነጋገር»።
04 ምሳሌ 12:22
እግዚአብሔር ሀሰተኛ ከንፈሮችን ይጠላል፣ በእውነተኛነት በሚኖሩ ሰዎች ግን ደስ ይለዋል፡፡
አካሄዱ ንጹሕ የሆነ፣ ጽድቅን የሚያደርግ ከልቡ እውነትን የሚናገር፤
06 ምሳሌ 12:19
እውነተኛ ከንፈሮች ለዘላለም ይኖራሉ፣ ሀሰተኛ ከንፈር ግን ለቅጽበት ብቻ ነው፡፡
07 ዮሐንስ 8:32
እውነትን ታውቃላችሁ፤ እውነትም ነጻ ያወጣችኋል” አላቸው።
08 ቆላስይስ 3:9
አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር አውልቃችሁ ስለ ጣላችሁ፣ አንዳችሁ በሌላው ላይ አትዋሹ።
እንግዲያስ አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈርህንም ከውሸት ጠብቅ፡፡
10 1ኛ ጴጥሮስ 3:10
ስለዚህ «ሕይወትን የሚወድና መልካም ቀኖችን ሊያይ የሚፈልግ ምላሱን ከክፉ፣ ከንፈሮቹንም ተንኰል ከመናገር ይከልክል።
11 ምሳሌ 8:7
አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡