ስለ ምላስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ምላስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ያዕቆብ 3:5
እንዲሁም አንደበት ትንሽ የሰውነት ክፍል ሆኖ፣ በታላላቅ ነገሮች ይኵራራል። ጫካ የቱንም ያህል ሰፊ ቢሆን፣ በትንሽ እሳት ፍንጣሪ እንደሚቃጠል ልብ አድርጉ!
02 ምሳሌ 18:21
ሞትና ሕይወት በምላስ ላይ ናቸው፣ የሚወዱትም ፍሬዋን ይበላሉ፡፡
03 ያዕቆብ 3:6
አንደበትም እንዲሁ እሳት ነው፤ ሰውነትን ሁሉ የሚያረክስና የሕይወትንም መንገድ የሚያቃጥል፣ እርሱ ራሱም በገሃነም እሳት የሚቃጠል ሰውነታችን ብልቶች መካከል ያለ ኃጢአተኛ ዓለም ነው።
04 ያዕቆብ 1:26
አንድ ሰው ሃይማኖተኛ ነኝ እያለ፣ አንደበቱን ግን ባይቆጣጠር፣ ልቡን ያስታል፤ ሃይማኖቱም ከንቱ ነው።
05 ምሳሌ 21:23
አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ሰው ራሱን ከመከራ ይጠብቃል፡፡
06 ምሳሌ 15:4
ፈዋሽ ምላስ የሕይወት ዛፍ ነው፣ አታላይ ምላስ ግን መንፈስን ይሰብራል፡፡
07 ኤፌሶን 4:29
ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።