ስለ ለመናገር መዘግየት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ለመናገር መዘግየት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 1:19

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ፣ ይህን ዕወቁ። ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገዬ፣ ለመቆጣትም የዘገዬ ይሁን!

02 ምሳሌ 10:19

በብዙ ቃላቶች ውስጥ ኃጢአት ሳይኖር አይቀርም፣ ለሚናገረው ነገር ጥንቃቄ የሚደርግ ሰው ግን ጥበበኛ ነው፡፡

03 ምሳሌ 17:28

ሞኝ እንኳ ዝም ሲል ጥበበኛ እንደሆነ ይታሰባል፤ አፉንም ዘግቶ ዝም ሲል፣ እንደ ምሁር ይቆጠራል፡፡

04 መክብብ 5:2

ለመናገር እጅግ አትፍጠን፥ በእግዚአብሔር ፊት የትኛውንም ጉዳይ ለማቅረብ ልብህ እጅግ አይፍጠን። እግዚአብሔር በሰማይ ነው፥ አንተ ግን በምድር፤ ስለዚህ ቃልህ ጥቂት ይሁን።

05 ምሳሌ 29:20

በቃሎቹ የሚቸኩለውን ሰው ተመልክተሃል? ከእርሱ ይልቅ ለሞኝ የበለጠ ተስፋ አለው፡፡

06 ምሳሌ 18:13

ከማድመጡ በፊት የሚመልስ ሰው ሞኝነትና ዕፍረት ይሆንበታል፡፡

07 ምሳሌ 15:28

ጽድቅን የሚያደርግ ሰው ልብ መልስ ከመስጠቱ በፊት አጥብቆ ያስባል፣ የክፉ ሰዎች አፍ ግን ክፋትን ሁሉ ያጎርፋል፡፡

08 ምሳሌ 13:3

አፉን የሚጠብቅ ሕይወቱን ይጠብቃል፣ ከንፈሮቹን ያለ ልክ የሚከፍት ግን ይጠፋል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች