ስለ ማጉረምረም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ማጉረምረም የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ።
በማጉረምረማቸው ምክንያት የሞት መልአክ እንዳጠፋቸው፣እኛም አናጉረምርም።
ያለ ማጒረምረም እርስ በርሳችሁ በእንግድነት ተቀባበሉ።
ህዝቡ ያህዌ እየሰማ ስለ ችግሮቻቸው አጉረመረሙ፡፡ ያህዌ ህዝቡን ሰምቶ ተቆጣ፡፡ ከያህዌ ዘንድ እሳት መጥታ በሰፈሩ ዙሪየ ከነበሩ ሰዎች አንዳንዶችን በላች፡፡
ወንድሞች ሆይ፤ እንዳይፈረድባችሁ እርስ በርሳችሁ አታጉረምርሙ። ልብ በሉ፤ ፈራጁ በሩ ላይ ቆሞአል።
ደግሞ እንዲህ አለ፤ በእርሱ ላይ ያጕረመረማችሁትን ሰምቶታልና፣ እግዚአብሔር ማታ ሥጋ፣ ጠዋትም ምግብ እስክትጠግቡ ሲሰጣችሁ፣ ይህን ታውቁታላችሁ። አሮንና እኔ ምንድን ነን? የምታጕረመርሙት በእኛ ላይ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ ነው።”
”እኔን የሚነቅፈውን ይህን ክፉ ማህበረሰብ እስከ መቼ እታገሳለሁ የእስራኤል ሰዎች በእኔ ላይ ሲያጉረመርሙ ሰምቻለሁ፡፡
ታዲያ ማንም ሕያው የሆነ ሰው እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል? ማንም ሰው ስለ ኃጢአቱ ቅጣት እንዴት ሊያጉረመርም ይችላል?
እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ ሌላውን የሚከሱ፥ የራሳቸውን ክፉ ምኞት የሚከተሉ፥ ጉራ የሚነዙና ጥቅም ለማግኘትም ሰዎችን የሚክቡ ናቸው።
ማናቸውንም ነገር ሳታጉረምግሙና ሳትከራከሩ አድርጉ። ይህን በማድረግ ነውርና ነቀፋ የሌለባችሁ ታማኝ የአግዚአብሔር ልጆች ትሆናላችሁ። በዚህ በጠማናና በመጥፎ ትውልድ መካከል በዚህ ዓለም እንደ ደማቅ ብርሃን ታበራላችሁ።
ድንኳናቸው ውስጥ አጉረመረሙ ለያህዌም አልታዘዙም፡፡
ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ ‹‹እርስ በርስ ማጕረምረማችሁን ተዉት፡፡
እስራኤል ሰዎች ሁሉ ሙሴንና አሮንን ነቀፉ፡፡ መላው ማህበረሰብ እንዲህ አሏቸው፣ “በግብጽ ምድር ብንሞት ይሻለን ነበር፡፡ ውይም ምነው በዚህ በረሃ በሞትን ኖሮ!
እንዲህ አሉት፤ “እዚህ ያመጣኸንና በምድረ በዳ እንድንሞት ያደረግኸው በግብፅ መቃብር ታጥቶ ይህን ነግረንህ አልነበረምን?
በእነርሱ ላይ የሆኑት እነኚህ ነገሮች ምሳሌ እንዲሆኑልን የተጻፈው፣ የዘመን ፍጻሜ ለደረሰብን ለእኛ ትምህርት እንዲሆንልን ነው።