ስለ የሚያበረታቱ ቃላት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የሚያበረታቱ ቃላት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ኤፌሶን 4:29
ለማነጽ የሚያስፈልግ፥ ለሚሰሙትም ጸጋን የሚሰጥ ጠቃሚ ቃል እንጂ የማይረባ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።
02 ምሳሌ 12:25
በሰው ልብ ውስጥ የሚገኝ ጭንቀት ያዋርደዋል፣ መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል፡፡
03 1 ተሰሎንቄ 5:11
ስለዚህ አሁን እንደምታደርጉት ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ፣ አንዱም ሌላውን ያንጸው።
04 ዕብራዊያን 3:13
ይልቁንስ ከእናንተ ማንም በኃጢአት መታለል እልኸኛ እንዳይሆን ከዛሬ ጀምሮ በየዕለቱ እርስ በርሳችሁ ተበረታቱ።
05 ምሳሌ 16:24
ደስ የሚያሰኙ ቃላት የማር ወለላ ናቸው፣ ለነፍስ የሚጣፍጡ አጥንትንም የሚፈውሱ ናቸው፡፡
06 ምሳሌ 25:11
በጥንቃቄ የተመረጠ ቃል መናገር፣ በብር ላይ እንደተቀረጻ የወርቅ ንድፍ ነው፡፡
07 ኢሳይያስ 50:4
የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፣ እንደ ተማሪዎችም ትሰማ ዘንድ ጆሮዬን ያነቃቃል።
08 ቆላስይስ 4:6
ለእያንዳንዱ ሰው እንዴት መመለስ እንዳለባችሁ እንድታውቁ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደ ተቀመመ በጸጋ ይሁን።
09 ምሳሌ 15:23
ሰው ተገቢ የሆነ መልስ ሲሰጥ ደስታን ያገኛል፤ የጊዜው ቃል ምንኛ መልካም ነው!