ስለ በክንፎቹ ሥር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ በክንፎቹ ሥር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በላባዎቹ ይጋርድሃል በክንፎቹም ሥር መሸሸጊያ ታገኛለህ፡፡ ታማኝነቱም ጋሻና መከታ ይሆንልሃል፡፡
በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ሥር ያድራል፡፡ ያህዌን፣ «መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ» እለዋለሁ፡፡
እንደ ዐይንህ ብሌን ጠብቀኝ፤ በክንፎችህ ጥላ ሥር ሰውረኝ፡፡
እግዚአብሔር ሆይ ማረኝ አቤቱ ማረኝ የመከራው ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ አንተን መጠጊያ አድርጌአለሁና፡፡ ጥፋት እስኪያልፍ ድረስ በክንፎችህ እጠለላለሁ፡፡
ኢየሩሳሌም፣ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ አንቺ ነቢያትን የምትገድዪ ወደ አንቺ የተላኩትን በድንጋይ የምትወግሪ! ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎቿ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን መሰብሰበ ብዙ ጊዜ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም!
እግዚአብሔር ሆይ፣ ታማኝነትህ እንዴት ክቡር ነው! የሰው ልጆች ሁሉ በክንፎችህ ጥላ ሥር መጠጊያ ያገኛሉ፡፡
አንተ ረዳቴ ነህና በክንፎችህ ጥላ ውስጥ ሐሤት አደርጋለሁ፡፡
ስለ ስራሽ እግዚአብሔር ይክፈልሽ፡፡ ከክንፉ በታች መጠጊያ ካገኘሽበት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ሙሉ ደመወዝሽን ተቀበይ” አላት፡፡
በማደሪያህ ለዘላለም ልኑር በክንፎችህም ጥላ ልከለል፡፡ ሴላ
ንስር ጎጆዋን እንደትጠብቅ፤ በጫጩቶቿም ላይ እንደምትረብብ፥ እነርሱን ለመያዝ ክንፎቿን እንደምትዘረጋ በክንፎቿም እንደምትሸከማቸው፥ እግዚአብሔር ክንፎቹን ዘርግቶ፥ ተሸከሞ ወሰዳቸው።
አንቺ ኢየሩሳሌም! ኢየሩሳሌም ሆይ! ነቢያትን የምትገድዪ፤ መልእክተኞችሽንም የምትወግሪ ነሽ፡፡ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ ሥር እንደምትሰበስብ እኔም ልጆችሽን ለመሰብሰብ ስንት ጊዜ ፈለግሁ፡፡ እናንተ ግን አልፈለጋችሁም፡፡
ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።
በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋል፡፡
ያህዌ ይጠብቅሃል፤ ያህዌ በቀኝህ በኩል ይከልልሃል፡፡