ስለ ትጋት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ትጋት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ምሳሌ 12:24
የትጉ ሰዎች እጅ ይገዛል፣ ሰነፍ ሰዎች ግን ለጉልበት ስራተኝነት ታልፈው ይሰጣሉ፡፡
02 ምሳሌ 10:4
የሰነፍ እጅ ድሃ ታደርጋለች፣ የትጉ እጅ ግን ብልጽግናን ታመጣለች፡፡
03 ቆላስይስ 3:23
የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው እንደምታደርጉ ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ በሙሉ ልባችሁ አድርጉት።
04 ምሳሌ 13:4
ሰነፍ ሰው ይመኛል ነገር ግን አንዳችም አያገኝም፣ የትጉ ሰው ምኞት ግን በሙላት ይረካል፡፡
05 መክብብ 9:10
በምትሄድበት በመቃብር ስፍራ ሥራ ወይም ገለጻ ወይም እውቀት ወይም ጥበብ በዚያ የለምና።
06 ምሳሌ 21:5
የትጉ ሰው እቅዶች ወደ ብልጽግና ይመራሉ፣ በችኮላ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ግን ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
07 ምሳሌ 22:29
በስራው ስልጡን የሆነውን ሰው አይተሃልን? በነገስታት ፊት ይቆማል፤ በተራ ሰዎች ፊትም አይቆምም፡፡