ስለ ሀብት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ሀብት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ምሳሌ 11:28
በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
02 1 ጢሞቴዎስ 6:17
በአሁኑ ዘመን ሀብታሞች ለሆኑት እንዳይታበዩ ንገራቸው፡፡ ደስ እንዲለን እግዚአብሔር በሚሰጠን እውነተኛ ብልጥግና እንጂ እርግጠኛ ባልሆነው በዚህ ምድራዊ ባለጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡
03 ምሳሌ 23:4-5
ባለጠጋ ትሆን ዘንድ ከመጠን በላይ አትልፋ፤ መቼ ማቆም እንዳለብህም ታውቅ ዘንድ ብልህ ሁን፡፡ አይንህን በገንዘብ ላይ በጣልክ ጊዜ፣ እርሱ ይጠፋል፣ በድንገት ክንፍ ያወጣል እንደ ንስርም ወደ ሰማይ እየበረረ ይሄዳል፡፡፤
04 መክብብ 5:10
ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
ነገር ግን ዛሬ እንደ ሆነ ለአባቶቻችሁ የማለላችሁን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ሀብት ለማከማቸት ጉልበት ሰጥቶአችኋል፥ እግዚአብሔር አምላካችሁን አስቡ።
06 ምሳሌ 22:1
ከብዙ ሐብት ይልቅ ጥሩ ስም ይመረጣል፣ ሞገስም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል፡፡
07 የማቴዎስ 6:24
! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡