ስለ አስራት ማውጣት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አስራት ማውጣት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

በቤቴ መብል እንዲኖር ሙሉ አስራት ወደጎተራ አስገቡ። “በቂ ቦታ እስከማይኖራችሁ ድረስ የሰማይን መስኮት ከፍቼ በረከትን ባላፈስስላችሁ በዚህ አሁን ፈትኑኝ” ይላል የሠራዊት ጌታ ያህዌ።

02 ምሳሌ 3:9-10

እግዚአብሔርን በሀብትህና በምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፣ ጎተራህ ሙሉ ይሆናል፣ ገንዳህ ደግሞ በአዲስ ወይን ጠጅ ተትረፍርፎ ይሞላል፡፡

አስራት ሁሉ፣ በምድሪቱ ላይ የበቀለ ሰብልም ሆነ ወይም የዛፍ ፍሬ የያህዌ ነው፡፡ ለያህዌ የተቀደሰ ነው፡፡

04 የማቴዎስ 23:23

እናንተ ግብዞች የአይሁድ የሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ፣ ከአዝሙድ፣ ከእንስላልና ከከሙን ዐሥራት ብታወጡም፣ የሕጉን ዋና ዋና ነገሮች ማለትም ፍትሕን፣ ምሕረትንና እምነትን ሥራ ላይ አታውሉም፡፡ ሌላውን ችላ ሳትሉ እነዚህን መፈጸም ነበረባችሁ፡፡

ይህ ለመታሰቢያነት ያቆምሁት ድንጋይ ወደ ፊት የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሁሉ ከዐሥር አንዱን እጅ ለአንተ እሰጣለሁ።"

06 ነህምያ 10:37

በየአመቱ ካመረትነው እህል ከበኩራቱ የተዘጋጀ ዱቄት ለካህናቱ ወደ ቤተ መቅደስ እናመጣለን፣ እንዲሁም ሌሎች የወይን፣ የወይራ ዘይትና የፍራፍሬ መስዋዕቶችንም ከበኩራቱ እናመጣለን፡፡ ካህናቱን ለሚረዱ የሌዊ ትውልዶች አስራቶችንም እናመጣለን፡፡

07 ሁለተኛ ዜና 31:5

ትእዛዙ እንደወጣም የእስራኤል ሕዝብ የእህሉን፥ የአዲሱን ወይን፥ የዘይቱን፥ የማሩን እንዲሁም ከእርሻው መከር ሁሉ በኩራት አትረፍርፈው ሰጡ፤ የሁሉንም ነገር አሥራትም አትረፍርፈው አመጡ።

ተዛማጅ ርዕሶች