ስለ ድህነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ድህነት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 12 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 19:17

ለድሃ ቸር የሆነ ሰው ለእግዚአብሔር ያበድራል፣ ለሰራውም ቸርነት መልሶ ይከፍለዋል፡፡

02 ምሳሌ 14:31

ድሀን የሚያስጨንቅ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ ለድሀ ቸርነትን የሚያሳይ ግን ፈጣሪውን ያከብራል፡፡

03 ምሳሌ 22:2

ሃብታምና ድሃ ሰዎች የሚጋሩት አንድ ነገር አለ፤ ይህም እግዚአብሔር የሁሉም ፈጣሪ መሆኑ ነው፡

04 1ኛ ሳሙኤል 2:7

እግዚአብሔር ድሃ ያደርጋል፥ ባለጸጋም ያደርጋል። እርሱ ያዋርዳል፥ ደግሞም ከፍ ያደርጋል።

ያህዌ ለተበደሉ እንደሚፈርድ ለችግረኛውም ፍትሕ እንደሚሰጥ ዐውቃለሁ፡፡

06 ምሳሌ 30:8-9

ከንቱነትንና ውሸትን ከእኔ አርቅ፡፡ ድህነትንም ብልጽግናንም አትስጠኝ፣ የሚያስፈልገኝን መብል ብቻ ስጠኝ፡፡ ብዙ ሃብት ካለኝ፣ አንተን ከድቼ “እግዚአብሔርን ማን ነው?” እላለሁና፣ ድሃ ከሆንኩኝ ደግሞ እሰርቃለሁ፣ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁና፡፡

07 ምሳሌ 13:23

የድሆች እርሻ ያልታረሰም ቢሆን ብዙ ምግብ ሊያመርት ይችላል፣ ነገር ግን በፍትህ መጓደል ምክንያት ተጠራርጎ ይወሰዳል፡፡

08 ምሳሌ 17:5

በድሃ የሚቀልድ ሰው ፈጣሪውን ይሰድባል፣ በጥፋትም የሚደሰት ከቅጣት አያመልጥም፡፡

09 ምሳሌ 31:20

እጇን ለድሆች ትዘረጋለች፤ ለተቸገሩትም እጆቿን ትዘረጋለች፡፡

10 ሉቃስ 6:20

ከዚያ በኋላም ወደ ደቀመዛሙርቱ ተመለከተና፣ እንደዚህ አላቸው፣ “የእግዚአብሔር መንግሥት ለእናንተ ናትና፣ እናንተ ድሆች የተባረካችሁ ናችሁ፡፡

11 ምሳሌ 21:13

የድሆችን ጩኸት የማይሰማ ሰው፣ እርሱም ሲጮህ ማንም አይሰማውም፡፡

12 ምሳሌ 30:14

ጥርሳቸው ሰይፍ የሆነ፣ መንጋጋቸውም ካራ የሆነ ትውልድ ናቸው፣ ድሆችን ከምድር፣ ችግረኞችንም ከሰው ልጆች መካከል ያጠፉ ዘንድ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች