ስለ ረክቶ መኖር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ረክቶ መኖር የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 5 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ፊልጵስዩስ 4:11

ይህን የምለው ለራሴ ጥቅም አይደለም። ምክንያቱም በሁሉም ሁኔታ ባለኝ ነገር መርካትን ተምሬአለሁ።

02 1 ጢሞቴዎስ 6:6-8

ባለው ለሚረካ ግን እግዚአብሔርን መምሰል እጅግ ማትረፊያ ነው፡፡ ወደ ዓለም ምንም አላመጣንምና፣ አንዳችም ይዘን መሄድ አይቻለንም፡፡ ምግብ እና ልብስ ካለን ያ ይበቃናል፡፡

03 ዕብራዊያን 13:5

አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።

04 ምሳሌ 30:8-9

ከንቱነትንና ውሸትን ከእኔ አርቅ፡፡ ድህነትንም ብልጽግናንም አትስጠኝ፣ የሚያስፈልገኝን መብል ብቻ ስጠኝ፡፡ ብዙ ሃብት ካለኝ፣ አንተን ከድቼ “እግዚአብሔርን ማን ነው?” እላለሁና፣ ድሃ ከሆንኩኝ ደግሞ እሰርቃለሁ፣ የአምላኬንም ስም አሰድባለሁና፡፡

05 ፊልጵስዩስ 4:12-13

በማጣትም ሆነ በማግኘት እንዴት መኖር እንዳለብኝ ዐውቃለሁ። በማንኛውም መንገድ የመጥገብንና የመራብን፤ የማግኝትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን ነገር ማድረግ እችላለሁ።

ተዛማጅ ርዕሶች