ስለ ገንዘብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ገንዘብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
የገንዘብ ፍቅር የክፋት ሁሉ ሥር ነውና፡፡ አንዳንድ ሰዎች ይህን ሲመኙ ከእምነት ስተው ራሳቸውን በብዙ ሐዘን ጎዱ፡፡
! ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይጠላል ሌላውንም ይወዳል፣ ወይም ለአንዱ ይታዘዛል ሌላውን ደግሞ ይንቃል፡፡ እግዚአብሔርንና ሀብትን ማገልገል አትችሉም፡፡
አኗኗራችሁ ከገንዘብ ፍቅር የጸዳ ይሁን። እግዚአብሔር ራሱ፣ “እኔ ፈጽሞ አልተውህም፣ ደግሞም አልጥልህም” ስላለ፣ ባላችሁ ነገር ረክታችሁ ኑሩ።
እግዚአብሔርን በሀብትህና በምርትህ ሁሉ በኩራት አክብረው፣ ጎተራህ ሙሉ ይሆናል፣ ገንዳህ ደግሞ በአዲስ ወይን ጠጅ ተትረፍርፎ ይሞላል፡፡
ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ይተዋል፤ ሌላውን ይወዳል፤ አለበለዚያም ለአንዱ ራሱን የሰጠ ይሆናል፤ሌላውን ደግሞ ይንቃል። ስለሆነም ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።
በባለጠግነታቸው ላይ የሚታመኑ ሰዎች ይወድቃሉ፣ ጽድቅን የሚያደርጉ ግን እንደ ቅጠል ይለመልማሉ፡፡
ማንም ብርን የሚወድ በብር አይረካም፥ ማንም ብልጽግናን የሚወድ ሁልጊዜ ተጨማሪውን ይፈልጋል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው።
ለእነርሱም እንዲህ አላቸው፣ "ስግብግብነት ከሞላባቸው ምኞቶች ራሳችሁን ጠብቁ፣ ምክንያቱም የአንድ ሰው ሕይወት በሀብቱ ብዛት ላይ የተመሠረተ አይደለም"
ባለጠጎች ድሆችን ይገዛሉ፣ ተበዳሪም ለአበዳሪው ባርያ ነው፡፡
በአሁኑ ዘመን ሀብታሞች ለሆኑት እንዳይታበዩ ንገራቸው፡፡ ደስ እንዲለን እግዚአብሔር በሚሰጠን እውነተኛ ብልጥግና እንጂ እርግጠኛ ባልሆነው በዚህ ምድራዊ ባለጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው፡፡ በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡
ብልና ዝገት በሚበላውና ሌቦችም ሰብረው በሚሰርቁበት በምድር ላይ ሀብትን ለራሳችሁ አታከማቹ፡፡ ይልቁን ብልም ሆነ ዝገት በማያጠፋበት፣ ሌቦችም ሰብረው በማይሰርቁበት በሰማይ ሀብትን ለራሳችሁ አከማቹ፡፡ ሀብታችሁ ባለበት ልባችሁም ይገኛልና፡፡