ስለ መስጠት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ መስጠት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 15 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 2ኛ ቆሮንቶስ 9:7

እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ ስትሰጡ በሐዘን ወይም በግድ አይደለም።

02 ሉቃስ 6:38

ለሌሎች ስጡ፣ ለእናንተም የተጠቀጠቀ፣ የተነቀነቀ፣ በእቅፎቻችሁም ተርፎ የሚፈስ መልካም መስፈሪያ ተሰፍሮ ይሰጣችኋል፡፡ ለሌሎች ለመስፈር በምትጠቀሙበት በዚያው መስፈሪያ ለእናንተም ይሰፈርላችኋል፡፡"

ደካሞችን በሥራ እንዴት እንደምትረዱ፣ “ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ የተባረከ ነው” የሚለውንም የጌታ ኢየሱስን ቃል እንዴት እንደምታስታውሱ በሁሉም ረገድ አርኣያ ሆንኋችሁ።

04 ምሳሌ 11:24-25

ዘርን የሚዘራ አንድ ሰው አለ፣ እርሱ ይበልጥ ይሰበስባል፤ ሌላ ደግሞ የማይዘራ አለ፣ እርሱ ይደኸያል፡፡ ለጋስ ሰው ይበለጽጋል፣ ለሌሎች ውኃ የሚሰጥ ደግሞ ለራሱም ውኃ ያገኛል፡፡

05 የማቴዎስ 6:3-4

አንተ ግን ምጽዋት ስትሰጥ፣ የቀኝ እጅህ የሚያደርገውን የግራ እጅህ እንዲያውቅ አታድርግ፤ ይኸውም ምጽዋትህ በስውር የሚሰጥ እንዲሆንና ከዚያም በስውር የሚያይ አባትህ ዋጋህን እንዲከፍልህ ነው፡፡

06 ምሳሌ 3:27

ልታደርግ የሚቻልህ ሲሆን፣ ለሚገባቸው ሰዎች መልካምን ነገር ከማድረግ አትከልክል፡፡

07 2ኛ ቆሮንቶስ 9:6

ፍሬ ነገሩ ይህ ነው ፦ በጥቂት የሚዘራ በጥቂቱ ያጭዳል ፣ አትረፍርፎ የሚዘራ አትረፍርፎ ያጭዳል።

08 2ኛ ቆሮንቶስ 8:12

ይህን ስራ ለመስራት ጉጉት ካለ፣ አንድ ሰው በሌለው ሳይሆን ባለው ነገር ላይ ተመስርቶ ሲሰራ መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው።

09 1 ጢሞቴዎስ 6:18

በመልካም ሥራ ባለጠጎች እንዲሆኑ፣ መልካም የሆነውን እንዲያደርጉ ለማካፈልም ፈቃደኞች እንዲሆኑ ንገራቸው፡፡

በዚህ ፈንታ፥ እግዚአብሔር አምላካችሁ በባረካችሁ መጠን እያንዳንዱ እንደ ችሎታው ይስጥ።

11 የማቴዎስ 10:8

ሕሙማንን ፈውሱ፣ ሙታንን አስነሡ፣ ለምጻሞችን አንጹ፣ አጋንንትንም አስወጡ፣ በነጻ ተቀብላችኋል በነጻ ስጡ።

12 ሮሜ 12:8

የማጽናናት ስጦታ ያለው ያጽናና፤ የመስጠት ስጦታ ያለው በልግስና ያድርገው፤ የመምራት ስጦታ ያለው በጥንቃቄ ይፈጽመው፤ምህረት የማድረግ ስጦታ ያለው በደስታ ያድርገው።

13 1ኛ ዜና 29:14

"ሁሉ የተገኘው ከአንተ ነው፤ ለአንተም የሰጠንህ ከእጅህ የተቀበልነው ብቻ ነው። ታዲያ እንዲህ ያለ ቸርነት እናድርግ ዘንድ እኔ ማነኝ? ሕዝቤስ ማንኝ?

14 ሉቃስ 21:3-4

ስለዚህ እንዲህ አለ፣ "እውነት እላችኋለሁ፣ ይህች ድኻ መበለት ከሁሉም የበለጠ ሰጠች። እነዚህ ሁሉ የሰጡት ስጦታ ከተትረፈረፈ ሀብታቸው ነው። ይህች መበለት ግን በድኽነቷ መተዳደሪያዋን ሁሉ ሰጠች።"

15 ዕብራዊያን 13:16

ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው።

ተዛማጅ ርዕሶች