ስለ በጥበብ መመላለስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ በጥበብ መመላለስ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ቆላስይስ 4:5

በውጪ ካሉት ጋር በጥበብ ተመላለሱ፤ ዘመኑንም ዋጁ።

02 ኤፌሶን 5:15-16

ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።

03 ያዕቆብ 1:5

ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡

04 ምሳሌ 4:7

ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡

05 ቆላስይስ 1:9-10

ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን። ጌታን ደስ በሚያሰኝ መንገድ በሁሉም እንደሚገባ እንድትመላለሱ፤ በማናቸውንም መልካም ሥራ ፍሬ እንድታፈሩና በእግዚአብሔርም ዕውቀት እንድታድጉ እንጸልያለን።

06 ምሳሌ 3:5-6

በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡

07 ምሳሌ 9:10

የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡

08 ያዕቆብ 3:17

ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።

ጥበበኞች መሆን እንድንችል ዕድሜያችን ምን ያህል መሆኑን አስተምረን፡፡

10 ምሳሌ 2:6

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች