ስለ እውቀት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ እውቀት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ምሳሌ 1:7

እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ ነው፣ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ፡፡

02 ሆሴዕ 4:6

ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል። እናንተ ካህናት ዕውቀትን ጥላችኋልና እኔም እጥላችኋለሁ። እኔ አምላካችሁ ብሆንም ሕጌን ረስታችኋል፥ እኔም ልጆቻችሁን እረሳለሁ።

03 ምሳሌ 2:5

በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ፡፡

04 2ኛ ጴጥሮስ 3:18

ነገር ግን በጌታችንና በአዳኛችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ዕውቀት እደጉ፤ ለእርሱ አሁንም፣ ለዘላለምም ክብር ይሁን፤ አሜን!

05 ፊልጵስዩስ 1:9

ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ።

06 ምሳሌ 9:10

የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡

07 ቆላስይስ 2:3

የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።

08 ምሳሌ 18:15

የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፣ የጠቢብም ጆሮ ይፈልገዋል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች