ስለ ውሳኔ ማድረግ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ውሳኔ ማድረግ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 9 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ምሳሌ 16:9
ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፣ እግዚአብሔር ግን እርምጃውን ያቀናለታል፡፡
02 ምሳሌ 3:5-6
በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤ በመንገድህ ሁሉ እርሱን እወቅ፣ እርሱም መንገድህን ቀና ያደርገዋል፡፡
03 ያዕቆብ 1:5
ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡
04 ምሳሌ 19:21
በሰው ልብ ብዙ እቅዶች አሉ፣ የሚፈጸመው ግን የእግዚአብሔር ሃሳብ ነው፡፡
የሰውን አካሄድ የሚያጸና ያህዌ ነው በመንገዱም ደስ ይለዋል፡፡
06 ቆላስይስ 3:15
የአንድ አካል ክፍሎች ሆናችሁ የተጠራችሁት ለዚህ ሰላም ስለ ሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይንገሥ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
07 ምሳሌ 21:5
የትጉ ሰው እቅዶች ወደ ብልጽግና ይመራሉ፣ በችኮላ የሚያደርግ ሰው ሁሉ ግን ወደ ድህነት ይመጣል፡፡
08 ምሳሌ 14:8
የጠንቃቃ ሰው ጥበብ መንገዱን ማስተዋል ነው፣ የሞኞች ከንቱነት ግን ማታለል ነው፡፡
09 ሉቃስ 14:28
ከእናንተ አንድ ሰው ሕንጻ መሥራት ቢፈልግ ለማጠናቀቅ የሚያስፈልገውን ገንዘብ በመጀመሪያ ተቀምጦ የማይተምን ማን ነው?