ስለ ማስተዋል የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ማስተዋል የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 7 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 5:14

በሌላ በኩል ደግሞ ጠንካራ ምግብ ግን መልካምንና ክፉውን መለየት ለተማሩና ትክክል የሆነውን ካልሆነው የመለየት ልምድ ላላቸው ትልልቅ ሰዎች ነው።

02 ፊልጵስዩስ 1:9-10

ፍቅራችሁ በዕውቀትና በሙሉ መረዳት የበለጠ እንዲበዘላችሁ እጸልያለሁ። ይህን የምጸልይበት ምክንያት የተሻለውን ነገሮችን መርምራችሁ እንድታውቁ እንዲሁም ክርስቶስ ተመልሶ በሚመጣበት ቀን ንጹኃንና ነውር የሌለባችሁ ሆናችሁ እንድትገኙ ነው።

03 1ኛ ዬሐንስ 4:1

ወዳጆች ሆይ! መንፈስን ሁሉ አትመኑ፣ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር መሆናቸውን መርምሩ፣ ምክንያቱም ብዙ ሃሰተኛ ነቢያት ወደ ዓለም ገብተዋል፡፡

04 1ኛ ቆሮንቶስ 2:14

የእግዚአብሔር መንፈስ የሌለው ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ስለሚሆንበት አይቀበለውም ። በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም።

05 1ኛ ነገስት 3:9

ስለዚህ ክፉውንና በጎውን በመለየት ሕዝብህን በማስተዋል በትክክኛ ፍርድ ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብ ስጠኝ። ይህ ካልሆን ይህን ታላቅ ሕዝብህን ሊመራ ማን ይችላል?

06 ሮሜ 12:2

መልካም፥ተቀባይነት ያለውና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንድታውቁ በታደስ አዕምሮ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትከትሉ።

07 ምሳሌ 14:15

እውቀት አልባ ሰው ሁሉንም ነገር ያምናል፣ አስተዋይ ሰው ግን አካሄዱን ያስተውላል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች