ስለ ከላይ የሆነ ጥበብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ከላይ የሆነ ጥበብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 11 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።
ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡
ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል።
እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡
ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።
በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።
«ጥበብና ኃይል የእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም የተባረከ ይሁን።» ጊዜዎችንና ወቅቶችን ይለውጣል፤ነገሥታትን ይሽራል በዙፋናቸውም ነገሥታትን ያስቀምጣል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።
የክብር አባት፥የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን ለማወቅ የሚያስችላችሁን የጥበብ እና የመገለጥ መንፈስ እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤
እግዚአብሄር ከመጀመርያ ፈጠረኝ፣ በቀድሞ ዘመን የስራው መጀመርያ ነኝ፡፡ ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡
በእምነታቸው በሰሉት ሰዎች መካከል በጥበብ እንናገራለን፤ ነገር ግን የምንናገረው የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ከጊዜ በኋላ የሚሻሩትን የዚህን ዓለም ገዢዎች ጥበብ አይደለም። ይልቁን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን ያዘጃውን፥ ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን የጥበብ እውነት እንናገራለን።
እግዚአብሔር ወደ እርሷ የሚወስደውን መንገድ ያስተውላል፥ስፍራዋንም ያውቃል። ምክንያቱም እርሱ የምድርን ዳርቻ፥ ከሰማይም በታች ያለውን ሁሉ ያያል። እርሱ አስቀድሞ ለነፋስ ሃይል መጠንን አደረገ፥ ውኆችንም በስፍር ሰፈረ፥ እርሱ ለዝናብ ሥርዓትን፥ ለነጐድጓድ መብረቅም መንገድን አደረገ፥ በዚያን ጊዜ ጥበብን አያት፥ ገለጣትም አጸናት፥ በርግጥም መረመራት። ለሰዎችም፦ እነሆ፥ “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው” አለ።