ስለ ጥበብ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ ጥበብ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ያዕቆብ 1:5

ከእናንተ አንዱ ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ከፈለገ፣ በሚጠይቀው ላይ ሳይቈጣ በልግሥና የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይጠይቅ፡፡

02 ምሳሌ 2:6

እግዚአብሔር ጥበብን ይሰጣልና፣ እውቀትና ማስተዋል ከአንደበቱ ይወጣሉ፡፡

03 ምሳሌ 9:10

የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡

04 ቆላስይስ 2:3

የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የተሰወረው በእርሱ ነው።

05 1ኛ ቆሮንቶስ 1:30

በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና።

06 ምሳሌ 4:7

ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡

07 ያዕቆብ 3:17

ከላይ የሚመጣው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ከዚያም ሰላም ወዳድ፣ ጨዋ፣ ደግ፣ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላበት፣ ለሰዎች አድልዎ የማያደርግ ቅን ነው።

08 መክብብ 7:12

ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው።

09 ምሳሌ 3:13

ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡

10 ኤፌሶን 5:15-16

ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን፥እንደ ጥበብኞች እንዴት እንደምትኖሩ ተጠንቀቁ። ክፉዎች ስለሆኑ ዘመኑን ዋጁ።

11 ምሳሌ 16:16

ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡

12 ዳንኤል 2:21

ጊዜዎችንና ወቅቶችን ይለውጣል፤ነገሥታትን ይሽራል በዙፋናቸውም ነገሥታትን ያስቀምጣል። ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል።

ያህዌን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው ትእዛዙንም የሚጠብቁ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፡፡ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል፡፡

ተዛማጅ ርዕሶች