ስለ መረዳት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ መረዳት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 14 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
ጥበብን የሚያገኛት ሰው ደስተኛ ነው፣ እውቀትንም ያገኛል፡፡
ጥበብ እጅግ በጣም ጠቃሚ ናት፣ ስለዚህ ጥበብን አግኛት፣ ያለህን ሀብት ሁሉ ከፍለህ ማስተዋልን የራስህ አድርጋት፡፡
ጥበብን ብታደምጥና ልብህን ወደ እውቀት ብትመልስ፡፡ እውቀትን ለማግኘት ብትጣራና ድምጽህን ከፍ አድርገህ ለማስተዋል ብትጮህ፣
ከመመሪያህ ማስተዋል አገኘሁ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ሁሉ ጠላሁ፡፡ ኖን
በሙሉ ልብህ በእግዚአብሔር ታመን፣ በራስህም ማስተዋል ላይ አትደገፍ፤
ከወርቅ ይልቅ ጥበብን ማግኘት ምንኛ ይበልጣል፡፡ ከብርም ይልቅ ማስተዋል ይመረጣል፡፡
የቃልህ ፍቺ ያበራል አላዋቂዎችን አስተዋይ ያደርጋል፡፡
ለሰዎችም፦ እነሆ፥ “እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው” አለ።
የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡
ጥበብ በአስተዋይ ሰው ዘንድ ትኖራለች፣ በሞኞች መካከል እንኳ ራሷን ታሳውቃለች፡፡
ወንድሞች እና እህቶች፣በአስተሳሰባችሁ ልጆች አትሁኑ። ይልቁን ክፋትን በተመለከተ እንደ ሕፃናት ሁኑ። ነገር ግን በአስተሳሰባችሁ ይበልጥ የበሰላችሁ ሁኑ።
ሞኝ ሰው በማስተዋል ደስታን አያገኝም፣ በራሱ ልብ ውስጥ ያለውን ነገር በመግለጥ እንጂ፡፡
ከዚህም ፍቅር የተነሣ ስለ እናንተ ከሰማንበት ቀን ጀምሮ ለእናንተ ከመጸለይ አላቋረጥንም። በፈቃዱ ዕውቀት፣ በጥበብ ሁሉና በመንፈሳዊ ማስተዋል እንድትሞሉ እንጸልይላችኋለን።
ጥበብን የሚያገኝ ሕይወቱን ይወዳል፤ ማስተዋልንም ገንዘቡ ያደረገ መልካም ነገር ያገኛል፡፡