ስለ የምስጋና መሥዋዕት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ የምስጋና መሥዋዕት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
01 ዕብራዊያን 13:15
የስሙን ታላቅነት የሚናገሩ የከንፈሮቻችንን ፍሬ፣ ማለትም የምስጋና መሥዋዕቶችን ያለማቋረጥ በኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል።
የምስጋና መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ ያከብረኛል፤ መንገዱን ቀና ለሚያደርግ የእግዚአብሔር ማዳን አሳየዋለሁ፡፡
03 ዕብራዊያን 13:16
ደግሞም መልካም ማድረግንና እርስ በርስ መረዳዳትን አትርሱ፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚደሰተው እንደነዚህ ባሉ መሥዋዕቶች ነው።
ለአንተ የምስጋና መሥዋዕት አቀርባለሁ የያህዌንም ስም እጠራለሁ፡፡
05 ዮናስ 2:9
እኔ ግን፣ በምስጋና መዝሙር መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈጽማለሁ፡፡ ድነት ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡
ያኔ በዙሪያዬ ባሉ ጠላቶቼ ላይ ራሴ ከፍ ከፍ ይላል በድንኳኑም የደስታ መሥዋዕት እሠዋለሁ ለያህዌ እቀኛለሁ፤ እዘምርለታለሁም፡፡
የምስጋና መሥዋዕት ያቅርቡለት በዝማሬም ሥራውን ያውጁ፡፡
በበጐ ፈቃድ መሥዋዕት አቀርብልሃለሁ መልም ነውና ያህዌ ሆይ፣ ስምህን አመሰግናለሁ፡፡
09 ሆሴዕ 14:2
የኑዛዜ ቃላት ያዝና ወደ እግዚአብሔር ተመለስ። እንዲህም በሉት፦«የከንፈሮቻችንን ፍሬ ምስጋናችንን እንሰዋልህ ዘንድ፤ክፋታችንን አስወግድ፥በቸርነትም ተቀበለን።
ጸሎቴ በፊትህ እንደ ዕጣን ይሁንልኝ ወደ አንተ ያነሣሁት እጄም እንደ ሠርክ መሥዋዕት ይቆጠርልኝ፡፡