ስለ ውዳሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ውዳሴ የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 8 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
እስትንፋስ ለው ሁሉ ያህዌን ያመስግን፡፡ ያህዌን አመስግኑ፡፡
ያህዌን ሁልጊዜ አመሰግናለሁ ምስጋናውም ዘወትር በአፌ ነው፡፡
ያህዌ ምስጋናው ታላቅ ነው ታላቅነቱም አይመረመርም፡፡
በፍጹም ልቤ ያህዌን አመሰግናለሁ ስለ ድንቅ ሥራዎችህም እናገራለሁ፡፡
05 ዕብራዊያን 13:15
የስሙን ታላቅነት የሚናገሩ የከንፈሮቻችንን ፍሬ፣ ማለትም የምስጋና መሥዋዕቶችን ያለማቋረጥ በኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይገባናል።
ያህዌ ይመስገን አምላካችንን በመዝሙር ማመስገን እንዴት መልካም ነው እርሱን ማመስገን ደስ ያሰኛል፤ ተገቢም ነው፡፡
ነፍሴ ሆይ፣ ያህዌ አመስግኚ የያህዌን ቅዱስ ስም በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ፡፡
አፌ በምስጋናህ ተሞልቶአል ስለ ክብርህም ቀኑን ሙሉ እናገራለሁ፡፡