ስለ አክብሮት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ስለ አክብሮት የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 13 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።

01 ዕብራዊያን 12:28

ስለዚህ፣ ሊናወጥ የማይችል መንግሥት ስለተቀብልን አምላካችንን እናመስግነው፣ ደግሞም እግዚአብሔርን ተቀባይነት ባለው በአክብሮትና በፍርሃት እናምልከው፣

02 ምሳሌ 9:10

የጥበብ መጀመርያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፣ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው፡፡

ምድር ሁሉ ያህዌን ትፍራው በዓለም ያሉ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጥ፡፡

04 መክብብ 12:13

ሁሉም ነገር ከተሰማ በኋላ የጉዳዩ መጨረሻ እግዚአብሔርን እንድትፈራውና ትዕዛዙን እንድትጠብቅ ነው፥ ይህ የሰው ሙሉ ተግባሩ ነውና።

05 ዕብራዊያን 12:29

ምክንያቱም አምላካችን የሚባላ እሳት ነው።

ያህዌን መፍራት የጥበብ መጀመሪያ ነው ትእዛዙንም የሚጠብቁ ጥሩ ማስተዋል አላቸው፡፡ ምስጋናውም ለዘላለም ይኖራል፡፡

07 ኢሳይያስ 8:13

ነገር ግን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን ቀድሱት፤ የሚያስፈራችሁና የሚያስደነግጣችሁም እርሱ ይሁን።

ጠብቁ የቤተመቅደሴን ቅድስና አክብሩ፡፡ እኔ ያህዌ ነኝ፡፡

ስሜን ለምትፈሩ ለእናንተ ግን ፈውስ በክንፎቹ የያዘ የጽድቅ ፀሐይ ይወጣላቸዋል። እናንተም ከጋጥ እንደተለቀቁ እንቦሳ እየቦረቃችሁ ትወጣላችሁ።

እስራኤል ሆይ፥ አሁንስ አምላክህን እግዚአብሔርን ትፈራ ዘንድ በመንገዱም ሁሉ ትሄድ ዘንድ፥ አምላክህንም እግዚአብሔርን ትውድድ ዘንድ፥ በፍጹም ልብህ፥ በፍጹምም ነፍስህ ታመልከው ዘንድ መልካምም እንዲሆንልህ

11 ምሳሌ 1:7

እግዚአብሔርን መፍራት የጥበብ መጀመርያ ነው፣ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሳጽን ይንቃሉ፡፡

እርሱ በቅዱሳኑ ጉባኤ መካከል እጅግ የተፈራ ነው፤ በዙሪያው ካሉትም ሁሉ ታላቅና አስፈሪ ነው፡፡

13 1ኛ ጴጥሮስ 1:17

ሳያዳላ በእያንዳንዱ ሰው ላይ እንደየሥራው የሚፈርደውን «አባት» ብላችሁ የምትጠሩት ከሆነ፣ በእንግድነት ዘመናችሁ እርሱን በማክበር ኑሩ።

ተዛማጅ ርዕሶች