ስለ ምስጋና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ስለ ምስጋና የሚናገሩ ለማንበብ፣ ለማሰላሰል፣ እና ለመሸምደድ የሚሆኑ 10 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች።
በምስጋና ወደ ደጆቹ፣ በውዳሴም ወደ አደባባዮቹ ግቡ፡፡ አመስግኑት ስሙንም ባርኩ፤
ወደ ፊቱ በምስጋና እንግባ በዝማሬም እናወድሰው፡፡
ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑት ምሕረቱም ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች፡፡
04 ኤፌሶን 5:20
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉም ነገር ሁልጊዜ እግዚአብሔር አብን አመስግኑ
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!
ቸር ነውና ያህዌን አመስግኑ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፡፡
07 1 ተሰሎንቄ 5:18
ስለ ሁሉም ነገር አመስግኑ፣ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ ነውና።
ቸር ነውና ምሕረቱም ለዘላለም ነውና ያህዌን አመስግኑ፡፡
09 ቆላስይስ 3:17
በእርሱ እግዚአብሔር አብን እያመሰገናችሁ በቃልም ሆነ በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
10 ፊልጵስዩስ 4:6
ስለ ሁሉም ነገር በጸሎት፤ በልመናና በምስጋና ለእግዚአብሔር አስታውቁ እንጂ ስለምንም ነገር አትጨነቁ። ጌታ ቅርብ ነውና።